Save today for better future

About

የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ተግባር

  • የመመዝገቢያ ክፍያ፣ የዕጣ ክፍያ፣ መደበኛ ቁጠባ፣ መደበኛ ያልሆነ ቁጠባ፣ የአገልግሎት ክፍያዎችንና ሌሎች ገቢዎችን ከአባላት መሰብሰብ፣
  • በየጊዜው እንደአስፈላጊነቱ ዕጣ አዘጋጅቶ መሸጥ፣
  • በብድር መመሪያው መሠረት የብድር አገልግሎት መስጠት፣ ተበዳሪ አባላት ገንዘባቸውን በአግባቡ መጠቀም ይችሉ ዘንድ ተገቢውን ምክር፣ዕገዛ፣ ክትትል፣ ትምህርት መስጠት፣ ለብድር የተሰጠው ገንዘብ በወቅቱ ከነወለዱ እንዲመለስ አስፈላጊውን መፈጸም፣
  • በቁጠባ ሂሳብ ለተቀመጠ ገንዘብ ተገቢውን ወለድ ማሰብ፣
  • ለማህበሩ ጥቅም በሚያስገኝ ቦታ ገንዘብ ማስቀመጥ፣
  • መደበኛ ያልሆነ ቁጠባውን ግለሰቦች ወጪ ለማድረግ በጠየቁ ጊዜ ማስተናገድ፣
  • ተከታታይ ትምህርት፣ መረጃና ሥልጠና ለአባላት፣ ለአመራር አካላት፣ ለቅጥር ሰራተኞች እና አባል ለሚሆኑ ግለሰቦች መሰጠት፣
  • ለስራው የሚያስፈልጉትን ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ማፍራትና ማስተዳደር፣
  • የኀብረት ሥራ ማኀበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን ወይም ፌደሬሽን አባል ለመሆን ዕጣዎችን መግዛት ቁጠባዎችን መቆጠብ፣
  • ማኅበሩ በተቋቋመበት አካባቢ ለሚኖረው ኅብረተሰብ ለውጥ የሚያመጡ/ጥቅም የሚያስገኙ የተለያዩ ዓይነት ብድሮችን ተረክቦ ማሰተዳደር፣
  • ለአባላት የተለያዩ አነስተኛ የመድን /Micro Insurance/ሽፋን አገልገሎት መስጠት፣
  • News

    Contact Us